በመኖሪያ አካባቢ ተሽከርካሪ ማቆሚያ ፈቃድ (RPP) ክለሳ
የታቀደው የ RPP ፕሮግራም
ካውንቲው የመኖሪያ ፈቃድን የመኪና ማቆሚያ ግምገማን በማካተት በየካቲት 2021 መደበኛ ስብሰባው በሕዝብ ፣በአማካሪ ኮሚሽኖች እና በካውንቲ ቦርድ ከግምት ውስጥ እንዲገባ የታቀደ ፖሊሲን አቅርቧል።
ቦርዱ የሚያቀርበው የታቀደው ፕሮግራም በዚህ በተሻሻለው የንፅፅር ሰንጠረዥ ውስጥ ካለው የአሁኑ ፕሮግራም ጋርእንዴት እንደሚወዳደር ይመልከቱ- በአማርኛ
የኮሚሽኑ ችሎቶች
ሰኞ ጃንዋሪ 25 የአርሊንግተን የእቅድ ኮሚሽን እና የትራንስፖርት ኮሚሽን በመኖሪያ ፈቃድ ፓርኪንግ (አር.ፒ.ፒ.) መርሃግብር ላይ በቀረቡት ለውጦች ላይ የጋራ የሥራ ክፍለ ጊዜ አካሂደዋል ፡፡ የሥራ ክፍለ ጊዜ ቀረጻ እዚህ ይገኛል።(here).
ሰራተኞች በሚቀጥሉት የካቲት አማካሪ ኮሚሽን ስብሰባዎች ላይ በ RPP ፕሮግራም ላይ የታቀዱ ለውጦችን ያቀርባሉ፣ የህዝብ ተወካዮች እንዲናገሩ በተጋበዙበት-
- የትራንስፖርት ኮሚሽን-ሐሙስ የካቲት 4 ቀን ከሌሊቱ 7 ሰዓት (Transportation Commission)
- የእቅድ ኮሚሽን-ሰኞ የካቲት 8 ቀን 7 ሰዓት (Planning Commission)
የካውንቲ ቦርድ ችሎት
ቦርዱ ባቀረበው የፕሮግራም ለውጦች ላይ መደበኛ ስብሰባው ላይ የካቲት 20 ፣ 2021 ላይ ድምጽ ይሰጣል። ስብሰባውንእንዴት እንደሚመለከቱ እና ለመናገር ለመመዝገብ የካውንቲ ቦርድ ድረ-ገጽን ይጎብኙ (County Board web page).
የካውንቲው ሠራተኞች የአርሊንግተንን የመኖሪያ አካባቢ የተሽከርከሪ ማቆሚያ ፈቃድ (RPP) መርሃ ግብርን ዓላማ በመከለስ ላይ ናቸው፡፡ ይህም በ10 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያው ዋነኛ ክለሳ ሲሆን፣ የፕሮግራሙን ውጤታማነት፣ የተገልጋዮችን ልምድ እና ፍትሐዊነትን ለማሻሻል የሚያስችሉ ለውጦችን ታሳቢ ለማድረግ ዕድል ይሰጣል፡፡
በመንገድ ላይ ተሽከርካሪ ማቆም ካውንቲው በበርካታ መንገዶች ላይ የሚያመቻቸው ጠቃሚ የማኅበረሰብ አገልግሎት ሲሆን፣ ይህም ለሕዝቡ የሚቻለውን ያህል መልካም አገልግሎት ለመስጠት በጥሩ ሁኔታ ሊተዳደር ይገባዋል፡፡ በአርሊንግተን ለረጅም ጊዜ የቆየው የRPP መርሃ ግብር በ24 የመኖሪያ አካባቢዎች የመንገድ ላይ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎችን አጠቃቀም ያስተዳድራል፤ ግቡም ለካውንቲው መንገዶች ከተቀመጡት ግቦች አንጻር ለነዋሪዎች በቅርብ የሚገኙ እና አመቺ የመንገድ ላይ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎችን ለማበርከት ነው፡፡
በኦገስት 2017 በነበረ የሥራ ክፍለ ጊዜ፣ የካውንቲው ቦርድ የፕሮግራሙን ዓላማ እና ተግባራት በድጋሚ ለማየት የቀረበውን ዕቅድ አጽድቋል (ለመጨረሻ ጊዜ የተካሄደው የመርሃ ግብሩ ክለሳ ከ2003 እስከ 2005 የነበረውን ጊዜ የሸፈነ ነበር)፡፡ ከዚህም ሌላ ቦርዱ ይህ ክለሳ ለሚካሄድበት ጊዜ አሁን ያለውን በዞን የተከፋፈለ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ፈቃድ ጸንቶ እንዲቆይ እና አዳዲስ ማቆሚያዎች እንዳይመሰረቱ፣ ያሉት ማቆሚያዎች እንዳይሰረዙ ወይም ለውጥ እንዳይደረግባቸው የቀረበውን ዕቅድ አጽድቋል፡፡ አሁን ያሉት ገደቦች ይቀጥላሉ፣ በመርሃ ግብሩ ተጠቃሚ ለመሆን ብዙ የሆኑ ነፍስ ወከፍ ቤተሰቦች የመረጃ ጽሑፎች የመጠየቅ መብት አላቸው፡፡

ይህ ካርታ የRPP ገደቦች ተፈጻሚ የሚሆንባቸውን ስፍራዎች ያሳያል (ከየካቲት 2019 ጀምሮ)፡፡
የRPP መርሃ ግብር በመላው ካውንቲ በተለያዩ አካባቢዎች ይሰራል፤ በ2017 የበጀት ዓመት፣ ከሞላ ጎደል 9,300 ቤተሰቦች ገደብ በሚሠራባቸው ሰዓታት ተሽከርካሪ የማቆም ፈጋድ ማግኛ ማቴሪያሎች ለማግኘት ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡ በመንገድ ላይ ተሽከርካሪ ማቆም ለርካታ ነዋሪዎች ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጠው ሕዝባዊ ጥቅም ነው፡፡ በእነዚህም ምክንያቶች፣ ሠራተኞች በተለያዩ ዘዴዎች ከሕዝቡ ጋር ለመወያየት ዕቅድ ይዘዋል፡፡ በዚህ ዓይነቱ ውይይት የተሰበሰቡ መረጃዎች፣ በሌሎች የመረጃ መሰብሰቢያ እና ትንታኔ መንገዶች ከተገኙት ጋር ተዳምረው፣ ቦርዱ ለሚያጸድቀው ማሻሻያ በውሳኔ ሃሳብነት የሚቀርበው መርሃ ግብር አካል ይሆናሉ፡፡
የክለሳ ሂደት የጊዜ ሰሌዳ
ይህ ምስል በፀደይ 2020 ይጠናቀቃል ተብሎ የሚገመገሙትን አምስት የግምገማው ሂደት ያብራራል ፡፡

አርፒፒ የጊዜ ሰሌዳ
የማህበረሰብ ተሳትፎ
ከ1600 በላይ ተሳታፊዎች በአርሊንግተን መንገድ ላይ መኪና ማቆም ላይ አስተያየታቸውን በካውንቲው ኦንላይን አስተያየት መስጫ ቅጽ ላይ በጁን እና ጁላይ 2018 ላይ አስፍረዋል። አስተያየት መስጫ ቅጹ የተዘጋጀው በ እንግሊዝኛ፣ ስፓኒሽ፣ እና አማርኛ ነበር።
ሰራተኞች በተጨማሪ የፓፕ አፕ ሁኔታዎችን በጁን 2018 ላይ በሚከተሉት ቦታዎች በማዘጋጀት በካውንቲው ሁሉ በተለያዩ ቦታዎች አስተያየቶችን ሰብስበዋል እንዲሁም ጥያቄዎችን መልሰዋል፥
- ኮሎምቢያ ፓይክ ብሉዝ ፌስቲቫል – ቅዳሜ፣ ጁን 16, 2:30 — 4:30 ፒኤም
- ኮሎምቢያ ፓይክ ብሉዝ ፌስቲቫል – ቅዳሜ፣ ጁን 23, 10:00 — 11:30 ኤኤም
- ሴኮያ – ሰኞ፣ ጁን 25, 12:30 – 2:30 ፒኤም
- ክሪስታል ሲቲ የገበሬዎች ገበያ – ማክሰኞ፣ ጁን 26, 4:30 — 6:30 ፒኤም
- ሊ ሃሪሰን የገበያ ማእከል – እሮብ፣ ጁን 27, 5:30 — 7:00 ፒኤም
- ሺርሊንግተን ቤተ መጽሃፍት – ሃሙስ፣ ጁን 28, 4:30 — 6:30 ፒኤም
በበልግ 2018 ሶስት ህዝባዊ መድረኮች በመኖሪያ የማቆሚያ ሁቤታ ሁኔታ ዙርያ በሚከተሉት ቦታዎች ተካሄደዋል፥
- ኪይ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት — እሮብ፣ ኖቬምበር 14 ከ 7:00 እስከ 8:30 ፒኤም
- አውሮራ ሂልስ የማህበረሰብ ማእከል — ሃሙስ፣ ኖቬምበር 29 ከ 6:00 እስከ 7:30 ፒኤም
- ድሪው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት — ቅዳሜ፣ ዲሴምበር 8 ከ 10:30 ኤኤም እስከ 12:00 ፒኤም