በአጠቃላይ፣ ሰራተኞቻችን ከበጋ 2018 ጀምሮ የመኖሪያ አካባቢዎች ውስጥ የመንገድ ላይ መኪና ማቆም በተመለከተ ህዝቡን በመጠየቅ ጀመሩ። ተከታታይ በሆኑ ቅጽበታዊና እና ጊዜያዊ ዝግጅቶች እና ኦንላይን አስተያየት መስጫ ቅጽ በመጠቀም፣ ሰራተኞቻችን ስለ RPP ዋና ፍሬ ሐሳቦችን ከ-1,600-በላይ ምላሾችን ሰብስበዋል።
በልግ 2018 ላይ፣ የተለዩት ፍሬ ሐሳቦች ላይ 200 ሰዎች ገደማ በተገኙበት ሰራተኞቻችን ተከታታይ የሆኑ ሶስት የማህበረሰብ ፎረሞችን አዘጋጅተው ነበር (ስለ ፎረሞቹ ተጨማሪ ዝርዝር ለማግኘት እዚህ፣ ይመልከቱ)። ፎረሞቹ ሕዝቡ መርሀግብሩ ላይ ምን ይሰራል እና ምን አይሰራም ብሎ እንደሚያስብ፣ የመስማሚያ እና የማይስማሙበት ጉዳዮች ለመለየት፣ እና የመጀመሪያ የሕዝብ ግብዓት ወቅት ያልታዩ ተጨማሪ ርእሶችን ለመለየት ለሰራተኞቻችን ጠቅሞአቸዋል።
ፎረሞቹ ላይ የተገኙት አስተያየቶች በመጠቀም፣ ጸደይ 2019 ላይ ሰራተኞቻችን ከአማካሪ ጋር በመሆን የአባወራ ቤተሰብ የዳሰሳ ጥናት አዘጋጅተው ነበር። የዳሰሳ ጥናት ግብዣዎች 60,000 የሚሆኑ የካውንቲ መኖሪያ ቤቶች ጋር ተልከው ነበር፣ እና 4,500 ገደማ የሚጠጉ ነዋሪዎች ስለ RPP መርሀግብር ያላቸውን አመለካከቶች እንደዚሁም ስለ RPP መርሀግብር ስለወደፊቱ ያላቸውን ምርጫዎች በተመለከተ ጥያዌዎች ላይ መልስ ሰጥተዋል (ስለ ዳሰሳ ጥናቱ በተመለከተ ዝርዝር ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ)