የመኖሪያ ቤት የመኪና ማቆሚያ ፈቃድ Residential Permit Parking RPP

ስለ መርሀግብሩ ክለሳ 

የመርሀግብር ክለሳ ለምን ተጀመረ?

በካውንቲው ቦርድ ድጋፍ ካገኘ በኋላ፣ የካውንቲው አስተዳዳሪ የ RPP ክለሳ እንዲጀመር ያደረገው በሁለት ምክንያቶች የተነሳ ነው፦  

  1. ከዚህ ቀደም የነበሩት ጥቂት አመታት ውስጥ፣ ነዋሪዎች የ RPP ገደቦች እንዲደረግላቸው ባልተለመደ መልኩ ብዙ ቁጥር ያላቸው ጥያቄዎችን በፊርማቸው አቅርበዋል። ሆኖም ግን፣ በእነዚህ መንገዶች ላይ የቢሮ ሰራተኞቻችን ጥናት ሲያደርጉ ጊዜ፣ አብዛኛዎቹ የመርሀግብሩን መስፈርቶች አያሟሉም።   
  2. ካውንቲው አንድ የአርሊንግተን የመኖሪያ ሰፈር ውስጥ RPP ገደቦችን እንዲያደርጉ አድርጓል፣ ይሄ በመቀጠል በአቅራቢያው የሚገኙ ነዋሪዎችን አስቆጥቷል። በዚህ ሰፈር ውስጥ ስላሉት ገደቦችን በመደገፍ ወይም በመቃወም የተሰለፉ ነዋሪዎች ስለ መርሀግብሩ ፍትሃዊነት እና ዓላማ ላይ ለረጅም ጊዜ የቆየ አለመስማማቶች እንደነበራቸው ገልጸዋል።  

እነዚህ ክስተቶች የሚያመላክቱት ነዋሪዎቹ መርሀግብሩ ከታለመው አላማ ውጪ የመኪና መቆሚያ ስፍራዎችን መርሀግብሩ እንዲያስተዳድር ስለፈለጉ፣ እና በዚህም የተነሳ የመርሀግብሩ ክለሳ አስፈልጓል። 

የታለመውን RPP መርሀግብር መቅረጽ ላይ የመስራያ ቤታችን ሰራተኞች ህዝቡን ያሳተፉበት መንገድ እንዴት ነበር?

በአጠቃላይ፣ ሰራተኞቻችን ከበጋ 2018 ጀምሮ የመኖሪያ አካባቢዎች ውስጥ የመንገድ ላይ መኪና ማቆም በተመለከተ ህዝቡን በመጠየቅ ጀመሩ። ተከታታይ በሆኑ ቅጽበታዊና እና ጊዜያዊ ዝግጅቶች እና ኦንላይን አስተያየት መስጫ ቅጽ በመጠቀም፣ ሰራተኞቻችን ስለ RPP ዋና ፍሬ ሐሳቦችን ከ-1,600-በላይ ምላሾችን ሰብስበዋል።  

በልግ 2018 ላይ፣ የተለዩት ፍሬ ሐሳቦች ላይ 200 ሰዎች ገደማ በተገኙበት ሰራተኞቻችን ተከታታይ የሆኑ ሶስት የማህበረሰብ ፎረሞችን አዘጋጅተው ነበር (ስለ ፎረሞቹ ተጨማሪ ዝርዝር ለማግኘት እዚህ፣ ይመልከቱ)። ፎረሞቹ ሕዝቡ መርሀግብሩ ላይ ምን ይሰራል እና ምን አይሰራም ብሎ እንደሚያስብ፣ የመስማሚያ እና የማይስማሙበት ጉዳዮች ለመለየት፣ እና የመጀመሪያ የሕዝብ ግብዓት ወቅት ያልታዩ ተጨማሪ ርእሶችን ለመለየት ለሰራተኞቻችን ጠቅሞአቸዋል።      

ፎረሞቹ ላይ የተገኙት አስተያየቶች በመጠቀም፣ ጸደይ 2019 ላይ ሰራተኞቻችን ከአማካሪ ጋር በመሆን የአባወራ ቤተሰብ የዳሰሳ ጥናት አዘጋጅተው ነበር። የዳሰሳ ጥናት ግብዣዎች 60,000 የሚሆኑ የካውንቲ መኖሪያ ቤቶች ጋር ተልከው ነበር፣ እና 4,500 ገደማ የሚጠጉ ነዋሪዎች ስለ RPP መርሀግብር ያላቸውን አመለካከቶች እንደዚሁም ስለ RPP መርሀግብር ስለወደፊቱ ያላቸውን ምርጫዎች በተመለከተ ጥያዌዎች ላይ መልስ ሰጥተዋል (ስለ ዳሰሳ ጥናቱ በተመለከተ ዝርዝር ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ)

የታቀደው RPP መርሀግብር ከአሁኑ መርሀግብር እንዴት ሊለይ ይችላል? የታቀደው መርሀግብር፦

  1. የታቀደው RPP መርሀግብር ከአሁኑ መርሀግብር እንዴት ሊለይ ይችላል? 

የታቀደው መርሀግብር፦ 

  • ገደቦች ላይ በፊርማ ጥያቄ ማቅረብ እና መርሀግብሩ ላይ መቀላቀል የሚችሉ አባወራ ቤተሰቦችን ቁጥርን ያሳድጋል  
  • በ RPP ዞኖች ውስጥ የሚኖሩ የቤተሰብ አባወራዎች ሊያገኙት የሚችሉትን የመጨረሻውን ዓመታዊ ፈቃዶች ቁጥርን አባወራ ቤተሰቡ ከመንገድ-ውጪ የመኪና ማቆሚያ እንዳለው ወይም እንደሌለው ያገናኛል እና እያንዳንድ የቤተሰብ አባወራ ሊያገኗቸው የሚችሏቸውን የመጨረሻ ቁጥር ይቀንሳሉ። 
  • ለአጭር ጊዜ ጎብኚዎች እና አገልግሎት አማራጮች ተጨማሪ አማራጮችን ያቀርባል  
  • ለመጀመሪያ ደረጃ፣ መካከለኛ ደረጃ እና ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሰራተኞች እና የቡድን ቤቶች ላይ ለሚሰሩ ሰራተኞች የተወሰነ ቁጥር ያላቸውን አዲስ ፈቃዶችን ይሰጣል 
  • ለመርሀግብሩ አጠቃላይ የታክስ ድጋፍን ለማብቃት የመኪና ማቆሚያ እና የማለፊያ ክፍያዎችን ያሳድጋል ይሄ ሲደረግ ለዝቀተኛ ገቢ ላላቸው አባወራ ቤተሰቦች ቅናሽ ይሰጣል 
  • <li">በፊርማ ጥያቄ የማቅረብ ሂደትን “ከቦታ-ውጪ” ፈተናን በማስወገድ እና የመኪና ማቆሚያ የመያዣ ገደቦችን እና የፊርማ ማሰባሰቡን የሚደገፉ የአባወራ ቤተሰቦችን ድርሻ በማሳደግ ይቀይራል  </li">

ለተጨማሪ መረጃ፣ የታቀደውን መርሀግብር [አገናኝ] መግለጫ እና የአስተዳደር ቅድመ ሁኔታዎችን ይመልከቱ። [አገናኝ]። 

የመርሀግብሩ ዓላማ የተቀረው እንዴት ነው?

የመርሀግብሩ ዓላማ ለዓመታት በጣም የተስፋፋ ሆኗል። 1972 ላይ፣ የመኖሪያ ሰፈሮች ላይ ተጓዥ መንገዶኞች መኪና ከማቆም ለመከላከል አርሊንግተን RPP መርሀግብር አቋቁሞ ነበር። ሆኖም ግን፣ አንዳንድ ነዋሪዎች የሚኖሩበት መንገድ ላይ የ RPP ገደቦችን ከማግኘት፣ እና RPP ገደቦች ያለባቸው መንገዶች የማቆሚያ ፈቃድ ከማግኘት ከልክሏቸው ነበር፣ ይሄ ቢያንስ እስከ የመጀመሪያዎቹ 1990ዎቹ ድረስ ዘልቆ ነበር። 2002 እና 2003 ላይ፣ የካውንቲው ቦርድ የተጓዥ መንገደኛ የመኪና ማቆሚያ ችግር የሌለባቸውን መኖሪያ ቦታዎች ላይ አዲስ RPP ዞኖችን ፈጥሮ ነበር፣ እና አንዳንድ የአፓርታማ ሕንፃዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች የሚገቡ መኪናዎችን ልክ እንደ “ከሰፈር ውጪ ያሉ ቦታዎች” በማለት ፈርጀው ነበር። 

የታቀደው መርሀግብር ሁለቱንም የነዋሪ እና የነዋሪ-ያልሆኑ መኪና ማቆሚያዎችን ለፊርማ ማሰበሰብ ጥያቄዎች ከቦታ-ውጪ ፈተናን በማስቀረት፣ ለሁለቱም የምሽት እና የሳምንት መጨረሻ ቀናት ገደቦችን ማስቀመጥን በማስቀጠል እና ነዋሪዎች የቦታ ዕቅድ መጠቀም እግድን በማስቀጠል እና ፈቃድ ያላቸውን ሕንፃዎች RPP ፈቃዶችን ከማግኘት እንዳይጠቀሙ በማድረግ ያስተዳድራቸዋል።

የታቀደው መርሀግብር ነባሮቹን ዞኖች ላይ ለውጥ ያመጣል?

መልሱ አዎ እንዲሁም አይደለም ነው። ገደቦቹ ዛሬ የተቀመጡባቸው ቦታዎች የሚገኙ መንገዶች እና ዛሬ የተቀሙጡባቸው ቦታዎች ሰዓታት ላይ እንዳሉ ይቆያሉ። ሆኖም ግን፣ በሜትር የሚሰራው የሁለት-ሰዓት መኪና ማቆሚያ እና እያንዳንዱ አባወራ ቤተሰብ የሚያገኛቸው የመጨረሻ ፈቃዶች ቁጥር ሁሉም RPP ዞኖች ላይ ይተገበራሉ። 

በተጨማሪም፣ ሁለት RPP ዞኖች እርስ በእርስ ድንበር የሚጋሩ ከሆነ፣ የታቀደው መርሀግብር ከሁለቱ ዞኖች አንዱ አቅጣጫ ላይ ምልክቱን በአንድ ህንፃ ይተካል ስለዚህ ከሁለቱ ዞኖች አንዱ ላይ ፈቃድ እና ማለፊያ ያላቸው ነዋሪዎች በእነዚያ መንገዶች ላይ ማቆም ይችላሉ። ለውጡ የዞኖቹ ጫፍ ላይ ለሚኖሩ ነዋሪዎች የተሻለ አማራጭ ያቀርብላቸዋል። በተጨማሪም በሁለቱም ዞኖች ላይ የዞን ፈቃዶች ጫፍ ላይ ለአንዳንድ አባወራ ቤተሰቦች የሚሰጠውን የአሁኑ ሰዓት የሚሰራውን አሰራር ያቃልላል።

የ RPP መርሀግብር ለውጦች የሚተገበሩት መቼ ነው?

በካውንቲው ቦርድ ተቀባይነት ካገኘ ጃንወሪ ላይ ነው፣ የታቀዱት ለውጦች ለመርሀግብሩ የሚተገበሩት ጁላይ 1፣ 2021 ጀምሮ ነው። አንድ አባወራ ቤተሰብ ሊያገኛቸው የሚችላቸው ዓመታዊ ፈቃዶች ላይ የሚጣሉ አዲስ ክፍያዎች እና ገደቦች ዓመታዊው የዕድሳት ክፍለ ጊዜ ጸደይ 2021 ጀምሮ ይጀመራሉ።  

ሁለት ለውጦች የ RPP የቁጥጥር ምልክቶችን መቀየር ይጠይቃሉ፦ 1) የሁለት-ሰዓት የመኪና ማቆሚያ መፍቀድ እና 2) ከሁለት ዞኖች ሕጋዊ የሆኑበት ፈቃዶች “የመሸጋገሪያ” መንገዶችን መፍጠር። ካውንቲው ሁሉንም RPP የቁጥጥር ምልክቶችን ከጁላይ 1፣ 2021 በፊት ለመቀየር ይሞክራል፣ ነገር ግን የስራው መጠን ለማጠናቀቅ ብዙ ጊዜ ሊወስድ ይችላል። ነባር ምልክቶቹ እስከሚቀየሩ ድረስ በቦታው ይኖራሉ። 

ለትምህርት ቤት ሰራተኞች ፈቃዶችን ለመስጠት የሚደረገው መርሀግብር ውሳኔ ያስፈልገዋል። 

ሰራተኞቻችን አዲስ መርሀግብር ላይ የሚደረገውን ስርዓቱን የጠበቀ ሽግግር ላይ እንዲያተኩሩ ለማድረግ፣ ሰራተኞቻችን አዲስ ገደቦች ወይም ነባሮቹ ገደቦች ላይ ለሚደረጉት ለውጦች የፊርማ ማሰባሰብ ጥያቄዎችን ከጁላይ ወይም ኦገስት 2021 መጨረሻ የሚደረገው ዓመታዊ የማደሻ ክፍለ ጊዜ ጀምሮ መቀበል ይጀምራሉ።

ብቁነት

አዲሱ ፖሊሲ የተጓዥ መንገደኛ መኪና ማቆሚያን ይገድባል?

በአብዛኛው። ሁሉም ተጓዥ መንገደኛዎች የሰዓት ገደብ የተጣለባቸው መንገዶች ላይ መኪና እንዳያቆሙ ይገደባሉ ምክንያቱም ፈቃዶችን ወይም ማለፊያዎችን ማግኘት አይችሉም።  

አንዳንድ የመጀመሪያ ደረጃ፣ መካከለኛ ደረጃ፣ እና ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሰራተኞች ፈቃዶችን እንዲያገኙ ይፈቀድላቸዋል በዚህ መሰረት RPP ዞኖች ላይ፣ ልክ እንደ የ RPP ዞኖች ውስጥ የሚገኙ የደባል መኖሪያ ተቋማት ሰራተኞች መኪና ማቆም ይችላሉ። ከዚህ ቀደም እንደነበረው፣ በ RPP ዞኖች ውስጥ የሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ላይ የሚሰሩ የግንባታ ሰራተኞች፣ ነገር ግን የኩባንያ ስም ያልተፃፈባቸውን መኪናዎችን የሚነዱ ከሆነ፣ የአጭር-ጊዜ ፈቃዶችን ማግኘታቸውን ይቀጥላሉ።

በዚህ መርሀግብር ላይ ለማሳተፍ ብቁ መሆን ላይ ምን ዓይነት ለውጦች ተከናውነዋል?

ብዙ የአባወራ ቤተሰቦች መንገዶቻቸው ላይ ገደቦች እንዲጣሉ በፊርማ በማሰባሰብ ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ፣ የሚፈቀድላቸው ከሆነ፣ በመርሀብሩ ላይ መሳተፍ ይችላሉ።  

ሁሉም የቤት ዓይነቶች ብቁ ይሆናሉ፣ ሆኖም በዚህ መልኩ የተገነቡ ሕንፃዎች አይጨምርም የቦታ ዕቅድ (Site Plan)፣ የተጣመሩ የመኖሪያ ልማቶች (Unified Residential Development)፣ የተጣመሩ የተቀላቀሉ የንግድ ልማቶች (Unified Commercial Mixed Use Development)፣ የንግድ ማዕከላት በቅጽ-ላይ የተመሰረቱ ኮድ (Commercial Centers Form-Based Code) የመጠቀም ፈቃድ፣ ወይም የመኖሪያ ሰፈር ቅጽ-ላይ የተመሰረቱ ካድ (Neighborhoods Form-Based Code) የመጠቀም ፈቃድ መስጠቶች ብቁ አይሆኑም። አብዛኛዎቹ አፓርታማዎች እና ኮንዶሚንየሞች እንደዚህ ዓይነት ፈቃዶችን በመጠቀም የተገነቡ ናቸው።

በቦታ ዕቅድ እና ሌሎች የተወሰኑ የአጠቃቀም ፈቃዶችን ያገኙ ሕንፃዎች ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎችን ከዚህ መርሀግብር ላይ እንዲወጡ ለምን ተደረገ?

የቦታ ዕቅድ እና የተወሰኑ የአጠቃቀም-ፈቃድ ዓይነቶች ያገኙ ቤቶችን የሚገነቡ አልሚዎች አርሊንግተን ዞን መስጠት ትዕዛዝ ከሚጠይቀው ይልቅ ጥቂት የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ቦታዎችን ለመገንባት ፈቃድ ሊያገኙ ይችላሉ፣ በተለይ እነዚያ ሕንፃዎች ከባቡር ጣቢያ አቅራቢያ ያሉ ከሆነ።  የእነዚህን ሕንፃዎች ነዋሪዎች ማስወጣት ገንቢዎች—ገንዘብ ለመቆጠብ ሲሉ—የወደፊት ነዋሪዎቻቸው ይፈልጉታል ብለው ከሚያምኑት ባነሰ መልኩ አነስተኛ የመኪና ማቆሚያ በመንገባት፣ እነዚህ  ነዋሪዎች የካውንቲው መንገዶች ላይ እንዲያቆሙ የሚገፋፋውን አመለካከት የሚያስቡበትን ዕድል ለመግታት ያግዛል። 

በአጠቃላይ፣ የአርሊንግተን ነዋሪዎችን የእነዚህ ሕንፃዎች ነዋሪዎች መንገድ ላይ ላይ መኪና የማያቆሙ ከሆነ በተጨማሪ አዲስ የከተማ ቤቶችን፣ አፓርታማዎችን፣ እና ኮንዶሚንየሞችን መገንባት ሊደግፉ ይችላሉ።  የቦታ-ዕቅድ እና የመጠቀም-ፈቃድ የተሰጣቸውን ህንፃዎች ነዋሪዎች ማስወጣት የቤት ግንባት ግቦችን ለማሳካት የቤት ግንባታ ማስፈለግ ላይ ያሉትን ተቃውሞዎችን ለመቀነስ ያስችላል።

ፈቃዶች እና ማለፊያዎች 

በታቀደው መርሀግብር ስር አንድ አባወራ ቤተሰብ ምን ያህል ፈቃዶችን ሊያገኝ ይችላል?

ማንኛውም (መተላለፊያ መንገድ፣ የመኪና ወደብ፣ ጋራጅ፣ ወይም የመኪና ማቆሚያ ስፍራ) ከመንገድ-የወጣ የመኪና ማቆሚያ ፈቃድ ያላቸው አባወራ ቤተሰቦች እስከ ሁለት ፈቃድ ድረስ ሊያገኙ ይችላሉ።   ከመንገድ-የወጣ የመኪና ማቆሚያ የሌላቸው አባወራ ቤተሰቦች እስከ ሶስት ድረስ ሊያገኙ ይችላሉ። 

ብቁ ለሆኑ አባወራ ቤተሰቦች ምን ዓይነት ፈቃዶች ይኖራሉ?

በታቀደው መርሀግብር ስር ነዋሪዎች መኪና ላይ ያተኮረ ፈቃድ፣ አንድ ፍሌክስፓስ (FlexPass)፣ ወይም ሁለቱንም በጋራ እስከ  ሁለት- ወይም ሶስት-ፈቃድ ማብቂያ ድረስ ሊያገኙ ይችላሉ። በአንድ አባወራ ቤተሰብ አንድ ፍሌክስፓስ ብቻ ይወሰናል።  

ልክ እንደዛሬው፣ ነዋሪዎቹ በተጨማሪም 20 የአጭር-ጊዜ-ጎብኚዎች ፈቃዶችን አምስት ጥቅሎች፣ እያንዳንዱ ለሶስት ቀናት ብቻ የሚሰሩ፣ ማመልከት ይችላሉ። 

በ RPP ዞን ውስጥ ቤት ያላቸው ሰዎች ነገር እዛ ውስጥ የማይኖሩ ሰዎች አንድ የቤት አከራይ ፈቃድ ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ።

ከመንገድ-ውጪ መኪና ማቆሚያ ላላቸው ነዋሪዎች አነስተኛ ፈቃዶችን ለምን መስጠት አስፈለገ?

አንዳንድ የአርሊንግተን ነዋሪዎች ብዙ ከመንገድ-ውጪ የመኪና ማቆሚያ ፈቃድ ያላቸው ነዋሪዎች RPP ገደቦችን ጥቅማጥቅሞችን መጠቀማቸውን ፍትሃዊ አይደለም ብለው ያስባሉ። በተጨማሪም፣ የዳሰሳ ጥናት ምላሾች እንደሚያመላክቱት RPP ገደቦች ያላቸው ሰዎች ካላቸው ከመንገድ-ውጪ የመኪና ማቆሚያ ፈቃድ ውጪ በአብዛኛው መንገድ ዳር የማቆም አዝማሚያ አላቸው። 

ሆኖም ግን፣ የአርሊንግተን ማስተር የትራንስፖርት ዕቅድ—አንድ ሰው ከመንገድ-ውጪ የመኪና ማቆሚያ ፈቃድ ይኑረው ወይም አይኑረው—ነዋሪዎች “ለመኪናዎቻቸው እና ለእንግዶቻቸው የመንገድ-ላይ መኪና ማቆሚያ የእነሱ መኖሪያ አጠቃላይ አቅራቢያ ላይ ለመጠቀም መኖር አለበት” የሚል ግምት አላቸው። 

በ RPP ዞን ውስጥ አንድ የቤተሰብ አባወራ ሊያገኛቸው የሚችላቸውን የመጨረሻ የፈቃዶች ቁጥር ሊያገኙት ከሚችሉት ከመንገድ-ውጪ የመኪና ማቆሚያ ፈቃድ ጋር በማጣመር፣ የታቀደው መርሀግብር በእነዚህ አመለካከቶች መካከል ለማስታረቅ የታቀደ ነው። በተጨማሪም ነዋሪዎች ያላቸውን ከመንገድ-ውጪ የመኪና ማቆሚያ ፈቃድ እንዲጠቀሙ ያበረታታል።

የመጨረሻውን ዓመታዊ ፈቃዶችን ቁጥር ከአራት (4) ወደ ሁለት (2) ወይም ወደ ሶስት (3) ማውረድ ለምን አስፈለገ?

ካውንቲው የአሁኑን በአንድ አባወራ ቤተሰብ ውስጥ አራት ዓመታዊ ፈቃዶችን (ሶስት-በመኪና-ላይ-የተወሰኑ ፈቃዶች እና አንድ ፍሌክስፓስ) እንዲተገበር በሚያደርግበት ወቅት፣ በዚያን ጊዜ በካውንቲው ውስጥ በሁሉም አባወራ ቤተሰቦች ሙሉ ለሙሉ ማለት ይችላል ከነበሩት መኪናዎች ቁጥር የበለጠ ስለነበር ሰራተኞቻችን ሆን ብለው መርጠውት ነበር። ሁሉም አባወራ ቤተሰቦች ማለት ይቻላል ካላቸው መኪናዎች ቁጥር በላይ የመጨረሻ ገደብ ማስቀመጥ ለአባወራ ቤተሰቦች ያላቸውን ከመንገድ-ውጪ የመኪና ማቆሚያ ፈቃድ እንዲጠቀሙ ብዙ አያበረታታም፣ የመጨረሻ ገደቡን ማሳነስ ብዙ መኪናዎች ያላቸው አባወራ ቤተሰቦች ያላቸውን ከመንገድ-ውጪ መኪና ማቆሚያ እንዲጠቀሙ፣ ለሌሎች ክፍት ቦታ እንዲተው ያበረታታል።  

አንዳንድ ነዋሪዎች የፈቃዶችን ቁጥር ያልተወሰነ ማድረግ ነገር ግን የፈቃዶችን ዋጋ መጨመር ነዋሪዎች መኖሪያቸው ላይ መኪና እንዲያቆሙ ያበረታታቸዋል ብለው ያስባሉ።  ሆኖም ግን፣ በ RPP መርሀግብር ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች ዋጋ ከመጨመር ይልቅ የሚሰጡትን የፈቃዶች ቁጥር መጠን በመቀነስ የመኪና ማቆሚያ ቦታን የማስተዳደር ስራው እንዲሰራ ይመርጣሉ።  

በተጨማሪም፣ በአንድ አባወራ ቤተሰብ የሚሰጡትን ፈቃዶች ቁጥር መገደብ በመስፋፊያ ብቁነት ሕጎች መሰረት RPP መርሀግብርን የሚቀላቀሉ አዲስ አባወራ ቤተሰቦች የሚመጣን የመኪና ማቆሚያ ቦታ የማግኘት ተጽእኖን ለመግታት ያግዛል።

በዝቅተኛው የፈቃድ ገደብ ምን ያህል አባወራ ቤተሰቦች ተጽእኖ ሊደርስባቸው ይችላሉ?

ዓመታዊ ፈቃዶችን የሚገዙ ብዙ አባወራ ቤተሰቦች አሁን እንደሚያገኙት ብዙ ፈቃዶችን ማግኘት አይችሉም። ከስራ ዓመት FY2019 RPP አስተዳደር ዳታቤዝ በተገኘው መዝገብ መሰረት፣ ሰራተኞቻችን እስከ 2,400 ነጠላ-የቤተሰብ የተነጠሉ ቤት ያላቸው አባወራ ቤተሰቦች (ወይም በዚያ ዓመት ላይ ፈቃዶችን የገዙ በነጠላ-ቤተሰብ የተነጠሉ ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ 44% የሚጠጉ ሁሉም አባወራ ቤተሰቦች) ማግኘት ከሚችሉት በላይ ዛሬ ብዙ ፈቃዶችን ይገዛሉ። 

ሰራተኞቻችን በ RPP ዞኖች ውስጥ የሚገኙ ታውንሃውሶች፣ ዱፕሌክሶች፣ አፓርታማዎች እና ኮንዶሚኖሞች ስለሚኖሩ ነዋሪዎች ትንሽ እርግጠኛ አይደሉም፣ ነገር ግን፣ ፈቃድ ከሚገዙ ነዋሪዎች ውስጥ ከ 300 እስከ 500 (ወይም18% እስከ 28%) ይጠጋሉ ብለው ይገምታሉ እና በታውንሃውስ እና ዱፕሌክስ የሚኖሩት በአሁኑ መርሀግብር ስር ልክ እንደሚያገኙት ብዙ ፈቃዶችን ለማግኘት አይችሉም ብለው ይገምታሉ። ፈቃድ ለሚገዙ አፓርታማ እና ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች፣ ከ 60 እስከ 250 (ወይም 3% እስከ 13%) ድረስ የሚጠጉት አሁን እንደሚያገኙት ብዙ ፈቃዶችን ለማግኘት አይችሉም። 

ከግዛት ውጪ ታርጋ ያለው መኪና ያላቸው ፈቃዶችን ማግኘት ይችላሉ?

አዎ። ልክ እንደ ዛሬ፣  በ RPP ዞን ውስጥ በሚገኝ አድራሻ መኪናው በአርሊንግተን ካውንቲ የገቢዎች ኮሚሽነር እስከተመዘገበ ድረስ፣ አንድ ነዋሪ ለዚያ መኪና ፈቃድ ማግኘት ይችላል። 

ለትምህርት ቤት ሰራተኞች ፈቃድ መስጠት ለምን አስፈለገ?

ካውንቲው የትምህርት ቤት ግንባታ ወይም የማስፋፋት ስራ ፈቃድ በሚሰጥበት ወቅት፣ አንዳንድ ነዋሪዎች በሰፈሩ ውስጥ የሚገኙ መንገዶች ላይ የትምህርት ቤት አስተማሪዎች እና ሰራተኞች መኪና እንዲያቆሙ ድጋፍ ሰጥተዋል ይሄም የሆነው ለኳስ ሜዳዎች እና ለአረንጓዴ ቦታዎች በቂ የሆነ ክፍት ቦታ ስለሚሰጥ ነው። ሆኖም ግን፣ በአሁኑ መርሀግብር ስር፣ የሰፈሩ ነዋሪዎች ቆይተው የ RPP ገደቦች እንዲቀመጡ በማድረግ የትምህርት ቤት ሰራተኞች በእነዚያ መንገዶች ላይ እንዳያቆሙ መከልከል ይችላሉ። አንዳንድ አስተማሪዎች እና ሰራተኞች የ RPP ፈቃዶች እንዲያገኙ መፍቀድ ተጨማሪ አረንጓዴ ስፍራዎች እና የሰፈሩ መንገዶች ላይ ተጨማሪ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች መካከል ያለውን ክርክር ያስታርቃል።  

በጥቅሉ፣ የ RPP ገደቦች የተጣለባቸው መንገዶች የስራ ቀናት ወቅት ከግማሽ ባነስ አይያዙም፣ ይሄም ማለት ቀን ላይ በመንገዱ ላይ እንዲያቆሙ በቂ የሆነ ቦታ አለ ማለት ነው። የአባወራ ቤተሰብ ዳሰሳ ጥናት ተሳታፊዎች የ RPP መንገዶች ላይ ማን እንዲያቆም እንደሚመርጡ በሚጠየቁበት ሰዓት፣ የትምህርት ቤት ሰራተኞች እና አስተማሪዎች ከአገልግሎት አቅራቢዎች እና ቤት አከራዮች ቀጥሎ በጣም ተመርጠዋል (ለተጨማሪ ዝርዝሮች እዚህ ላይ ጠቅ ያድርጉ)።

ጎብኚዎች

የጎብኚዎች ፈቃድ የመጨረሻው ቁጥር እና ዓይነት ይቀየራል?

አይ። አባወራ ቤተሰቦች  እስከ አምስት (5) ሃያ (20) ጥቅል የአጭር ጊዜ የጎብኚ ፈቃዶችን በዓመት ውስጥ ያገኛሉ። የፍሌክስፓስ ለመግዛት የሚመርጡ አባወራ ቤተሰቦች ለእንግዶች ፍሌክስፓሱን መስጠትም ይችላሉ። 

የታቀደው መርሀግብር በቤት ውስጥ የሚሰሩ ሰዎችን እንዴት ያስተናግዳል?

ከፍሌክስፓስ እና የአጭር-ጊዜ የጎብኚዎች ማለፊያ ተጨማሪ፣ የቤት ውስጥ አገልግሎት ለሚሰጡ ሰዎች በ RPP ዞኖች ላይ መኪና እንዲያቆሙ አማራጭ ይኖራል።  

ልክ እንደ ዛሬ፣ በ RPP ዞን ውስጥ የቤት ውስጥ አገልግሎት የሚሰጡ የድርጅቱ/የኩባንያ/ ስም በግልጽ የተፃፈባቸው መኪናዎች (ለምሳሌ፣ FedEx፣ Verizon፣ ወዘተ) ከገደቡ ነፃ ይሆናሉ። ጉድ-ኢን-ኦል-ዞኖች ፈቃዶች ለቤት ውስጥ የጤና እንክብካቤ ሰጪዎች፣ ማህበራዊ ሰራተኞች፣ እና ቤት ውስጥ የአገልግሎት ጥሪ ተቀብለው ዘውትር ለሚሰሩ ሌሎች ሰዎች ይኖራል። 

በስተመጨረሻ፣ የታቀደው መርሀግብር በጊዜያዊ ፈቃድ በ RPP ዞን ውስጥ የሚሰሩ የግንባታ ተቋራጮች (እና የኩባንያ አርማ ያለው መኪና የሌላቸው) ሲሰጥ የነበረው አገልግሎት መደበኛ እንዲሆን ይደርገዋል።

ጎብኚዎች ያለ ፈቃድ/ማለፊያ ለተወሰነ ጊዜ ያህል መኪና ማቆም ይችላሉ?

ምንም እንኳን ገደቦች የተቀመጡ ቢሆንም እስከ ሁለት ሰዓታት ድረስ በ RPP-የተገደቡ መንገዶች ላይ ያለ ፈቃድ ወይም ማለፊያ ማንኛውም ሰው መኪና ማቆም እንዲችል የታቀደው መርሀግብር ያስችላል። ለአርሊንግተን ካውንቲ ፖሊስ የጊዜ ገደቡን መተግበር ላይ ቀላል ለማድረግ፣ ያለ RPP ፈቃድ ወይም ማለፊያ መኪና የሚያቆሙ ሰዎች በ ፓርክሞባይል (ParkMobile) አገልግሎት ወይም የኢዚፓርክ (EasyPark) መሳሪያ በመጠቀም ክፍያ መክፈል አለባቸው። ምንም የመኪና ፓርክ ሜትሮች አይጫኑም፣ ነገር ግን የክፍያ ተመኑ ልክ እንደ ካውንቲው ሌሎች የአጭር-ጊዜ የመኪና ማቆሚያ ሜትሮች ክፍያ ( በአሁኑ ሰዓት በሰዓት $1.75) ተመን ተመሳሳይ ዋጋ ይከፍላሉ።

ክፍያዎች

ለፈቃዶች እና ማለፊያዎች የሚደረጉት ክፍያዎች ይቀየራሉ?

ለሁሉም የመኖሪያ ቤቶች ማለፊያዎች ክፍያዎቹ የመርሀግብሩን ወጪ ለመሸፈን እንዲጨምሩ ይደረጋሉ።   

ፍሌክስፓስ እና የአጭር-ጊዜ ጎብኚ የመጀመሪያው ጥቅል ማለፊያ ከአሁን ወዲያ ያለክፍያ አይሰጡም።  ብቁ ለሆኑ፣ የዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አባወራ ቤተሰቦች ፍሌክስፓስ፣ የአካራይ ማለፊያ፣ መኪና-ላይ የተወሰኑ ፈቃዶች፣ እና የአጭር-ጊዜ የጎብኚዎች ማለፊያ ላይ  50% ቅናሽ ይሰጣል። 

ክፍያዎቹ እያንዳንዱ ዓመት ላይ ይገመገማሉ እና መርሀግብሩን ለመተግበር በሚወጣው ወጪ መሰረት ሊጨምሩ ወይም ሊቀንሱ ይችላሉ። ለመጀመሪያ ዓመት፣ የታቀዱት ዋጋዎች የሚከተሉት ናቸው፦ 

  • ፍሌክስፓስ እና የአከራይ ማለፊያ፦ $40 
  • እንደ መኪናው ዓይነት የሚወሰን ፈቃድ፦ $40 ለመጀመሪያው ፈቃድ፣ $55 ለሁለተኛው።  ሶስት ፈቃዶችን ለሚያገኙ አባወራ ቤተሰቦች፣ ለሶስተኛው $65።   
  • የአጭር ጊዜ የጎብኚዎች ጥቅል፦ $5 ለመጀመሪያው ጥቅል እና $10 ለሚቀጥሉት እያንዳንዱ ተከታታይ አራት (4) ጥቅሎች።    
  • ጉድ ኢን ኦል ዞኖች ፈቃዶች፦ $40 
  • ጊዜያዊ የስራ ተቋራጭ ፈቃድ፦ $10 ለሶስት ወራት 
  • የትምህርት ቤት ሰራተኛ እና የደባል መኖሪያ ተቋማት ሰራተኛ ፈቃዶች፦ $40

ከአጠቃላዩ ታክስ ክፍያ አካል በማድረግ ለመርሀግብሩ ለምን መክፈል አይቻልም?

ዕቅዱ መርሀግብሩ በተጠቃሚዎች ክፍያ የታክስ አካል ሳይሆን፣ ሙሉ ለሙሉ እንዲሸፍን አድርጓል፣  ምክንያቱ ደግም የሚከተሉት ናቸው፦  

  1. RPP ብዙዎችን የሚገድብ እና አንዳንድ የሕዝብ አካላትን የሕዝብ ግብዓት ከመጠቀም የሚያግድ በበጎፈቃድ የሚሰራ መርሀግብር ነው። 
  2. በ RPP ዞን ውስጥ 10% የሚያህሉት ብቻ የካውንቲው አባወራ ቤተሰች ናቸው። 
  3. ምንም እንኳን ብቁነት መስፈርቶችን በማስፋት፣ የታቀደው መርሀግብር ለብዙ ነዋሪዎች የማይገኝ ይሆናል።

ዝቅተኛ-ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች እንዴት ይስተናገዳሉ?

ለሚከተሉት መርሀግብሮች ብቁ የሆኑ ነዋሪዎች የፍሌክስፓስ፣ የአከራይ ማለፊያ፣ እንደ መኪና ዓይነት የሚወሰን ፈቃድ፣ እና የአጭር-ጊዜ ጎብኚዎች ማለፊያ ጥቅል ላይ 50% ቅናሽ ይሰጣቸዋል፦ 

  • ተጓዳኝ የተመጣጠነ ምግብ ድጋፍ ፕሮግራም (SNAP) 
  • ሴቶች፣ ሕፃናት እና ልጆች (WIC) 
  • ለችግረኛ ቤተሰቦች ጊዜያዊ ድጋፍ (TANF) 
  • SSI/SSDI ተጓዳኝ የደህንነት ገቢ (Supplemental Security Income) 
  • ዝቅተኛ አቢ የቤት ኋይል አቅርብዖት ድጋፍ መርሀግብር (Low Income Home Energy Assistance Program) (LIHEAP), 
  • ሜድክኤድ 

ነዋሪዎች የብቁነት ማረጋገጫ ፈቃዶችን እና ማለፊያዎች የቡቁነት ማረጋገጫ ማቅረብ ያስፈልጋቸዋል። 

ፈቃዶችን እና ማለፊያዎችን በዋጋ መተመን ለምን አላስፈለገም ምክንያቱም በጣም የሚፈልጉባቸው ቦታዎች ላይ ብዙ እንዲያስከፍሉ እና ብዙም የማይፈልጉባቸው ቦታዎች ላይ ትንሽ እንዲያስከፍሉ?

ሌሎች የማህበረሰቡ ዓባላት እንዳሰቡት ሰራተኞቻችንም ይሆንን ከግምት ውስጥ አስገብተው ነበር።  

ሆኖም ግን፣ ሰራተኞቻችን ነዋሪዎችን መርሀግብሩ የመኪና ማቆሚያ ስራ እንዴት እንደሚተዳደር ሲጠየቁ ጊዜ፣ ከከፍተኛ ዋጋዎች ከመጠቀም ይልቅ የሚሰጡትን ፈቃዶችን ገደብ ማበጀት ነዋሪዎቹ መርጠዋል።   በተጨማሪም፣ የ RPP ፈቃድ እና የማለፊያ ዋጋዎችን ከፍላጎት ጋር በማገናዘብ መቀያየር መርሀግብሩን የተወሳሰበ ያደርገዋል እና ለመተግብር፣ ለማስቀጠል እና ለማሳተዳደር ብዙ ግብዓቶችን ይጠይቃል።

የታቀዱት የመርሀግብር ክፍያዎች አማራጭ የትራንስፖርት ዘዴዎችን ይደጉማል?

አይ፣ የታቀደው መርሀግብር ክፍያዎች የ RPP መርሀግብርን ብቻ ለማስተዳደር እና ለመተግበር የሚወጡትን ወጪዎች ለመሸፈን ይሰላሉ።

የመንገድ-ላይ ማቆሚያ መያዝ

እኔ የምኖረው RPP ዞን ውስጥ ነወ። ብዙ አባወራ ቤተሰቦች በፊርማ ጥያቄ ለማቅረብ እና መርሀግብሩ ላይ መቀላቀል ይችላሉ፣ በእኔ መንገድ ላይ የመኪና ማቆሚያ ማግኘት ከባድ አይሆንብኝም?

ሊሆን ይችላል። ይሄንን ጥያቄ መመለስ ከባድ ሊሆን ይችላል። 

  1. በታቀደው መርሀግብር ስር ብዙ አባወራ ቤተሰቦች ብቁ ቢሆኑም፣ ሁሉም ገደቦች እንዲጣሉ በፊርማ ማሰባሰብ ጥያቄ ላያቀርቡ ይችላሉ። በ 2019 በተደረገው የአባወራ ቤተሰብ የዳሰሳ ጥናት ላይ፣ በአፓርታማ ወይም ኮንዶሚንየም ከሚኖሩት 12% ያህል የሆኑት እና ከዚህ ቀደም በ RPP zone ያልኖሩት ብቻ የ RPP ገደቦችን እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፣ ወደ 37% ገደማ የሚጠጉ የታውንሃውስ ወይም ዱፕሌክስ ነዋሪዎች እና 17% የሚሆኑት የነጠላ-ቤተሰብ የተነጠሉ ቤቶች ነዋሪዎች ተመሳሳይ ምላሽ ሰጥተዋል።  
  2. የ RPP ገደቦች የሚፈልጉ ነዋሪዎች የፊርማ ማሰባሰብ ጥያቄ ለማቅረብ ለድጋፍ በቂ የሆኑ ጎረቤቶቻቸውን ሊያሳምኑ ወይም ላያሳምኑ ይችላሉ።  
  3. አንዳንድ ነዋሪዎች የካውንቲውን የመያዝ መስፈርቶች የማያሟሉ መንገዶች ላይ ገደቦች እንዲጣሉ የፊርማ ማሰበሰብ ጥያቄ ያነሳሉ፣ እና ይሄንን በማድረጋቸው የእነሱ አባወራ ቤተሰብ በ RPP ዞን ውስጥ አይካተትም። በቅርብ ዓመታት ውስጥ፣ 64% ገደማ የሚጠጉት የፊርማ ማሰባሰብ ጥያቄዎች የካውንቲ የሚፈቅድ RPP ገደቦች ያመጣሉ። 
  4. ገደቦቹ የሚጣሉ ከሆነ፣ በመርሀግብሩ ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ሰው አይገዛም ወይም ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው ፈቃዶችን አይገዛም።  
  5. በአንድ RPP ዞን ውስጥ አንድ አባወራ ቤተሰብ ሊያገኝ የሚችለውን የመጨረሻውን የፈቃድ ቁጥሮች መቀነስ ነዋሪዎች የመኪና ማቆሚያ ቦታቸውን፣ ጋራጃቸውን፣ የመኪና ወደቦቻቸውን ወይም መንገዳቸው በደንብ እንዲጠቀሙበት ያበረታታቸዋል።  ይሄ በመንገድ-ላይ የመኪና ማቆሚያ ክፍት ቦታዎች ነፃ ያደርጋል።

አንድ ሰውን ያለ ፈቃድ ወይም ማለፊያ ለሁለት ሰዓታት ያህል በ RPP ዞን ላይ መኪና እንዲያቆም ማድረግ መኪና ማቆሚያ ቦታ ማግኘትን አዳጋች አያደርገውም?

ሊሆን ይችላል። ሆንም ግን፣ ሰራተኞቻችን ያጠኑባቸው የ RPP ገደቦች የተጣለባቸው መንገዶች ላይ፣ ቀን ላይ የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ቦታዎች ከግማሽ ባነሰ የተያዙ ናቸው። ካውንቲው የመያዝ መረጃ የሰበሰበባቸው ያለ ፈቃድ ወይም ማለፊያ የሁለት-ሰዓት መኪና ማቆም አገልግሎት የሚሰጥባቸው ጥቂት መንገዶች ላይ፣ የመያዝ ሁኔታ በጥቂት መቶኛ ነጥቦች አንዳንድ ጊዜ ከፍተኛ ነው። ይሄ የሚያመላክተው ብዙ ክፍት ቦታዎች ገደብ የሚጣልባቸው ሰዓታት ላይ ይያዛሉ፣ ነገር ግን በመንገድ ካይ፣ የሁለት-ሰዓት የመኪና ማቆም ነፃ ነው፣ ስለዚህ ልክ እንደ መንገድ ላይ እንዳለው የመያዝ ሁኔታው ከፍተኛ አይሆንም። 

ማንኛውም ሰው ያለ ፈቃድ ወይም ማለፊያ መኪና እንዲያቆም መፍቀድ በ RPP ዞን ውስጥ ለሚጎበኙ ወይም በቤት ውስጥ ለሚሰሩ ሰዎች፣ የጎብኚ ማለፊያ ተግባራዊ በማይሆንበት ሰዓት፣ ሌላ አማራጭ ይሰጣል።   ቅርብ ያሉት ንግድ ተቋማት ጋር መሄድ የሚመርጡ አንዳንድ ሰዎች የተገደቡት መንገዶች ላይ ለሁለት ሰዓት ያህል መኪና ለማቆም ሊመርጡ ይችላሉ፣ ነገር ግን የመኪና ማቆሚያ ክፍያ ስለሚኖር፣ ሜትር ካላቸው መንገዶች ይልቅ የ RPP ገደቦች የተጣለባቸው መንገዶች ላይ መኪና ማቆም ከገንዘብ አንፃር አዋጭ አይሆንም። በተጨማሪም፣ ክፍያ ማስከፈል ለአርሊንግተን ካውንቲ ፖሊስ የሁለት ሰዓት ወሰንን እንዲተገብር ቀላል ይሆንለታል።

መርሀግብሩ ቤቴ ፊትለፊት መኪና እንዳቆም ዋስትና ይሰጣል?

አይ። የአንድ የተወሰነ መኖሪያ ቤት ነዋሪ ብቻ በዚያ ቤት ፊትለፊት እንዲያቆም መሞከር የመንገድ-ላይ መኪና ማቆሚያ መያዝን ቁጥር በጣም ዝቅተኛ ማድረግ ይጠይቃል፣ ይሄ የመንገድ ላይ መኪና ማቆሚያ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ ለመጠቀም አያስችልም፣  ፈቃድ ያለውን ማንኛውም ሰው በመንገድ ላይ እንዲያቆም በመፍቀድ፣ ለነዋሪዎች አመቺነትን ይሰጣል እና ጎብኚዎች የሚደርሱበት ቦታ ቅርብ ማቆም እንዲችሉ ያስችላል።  የመኪና ማቆሚያ ቦታ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል በካውንቲው የሚያዙ ናቸው እና ለአንድ አባወራ ቤተሰብ ብቻ መፍቀድ ከዛ ተልዕኮ ጋር የሚፃረር ይሆናል።

የታቀደው መርሀግብር አካለስንኩላን ላይ ምን አይነት ተጽእኖ ያሳድራል?

ልክ እንደ አሁኑ መርሀግብር፣ የታቀደው መርሀግብር አካለስንኩላን ላይ ምንም ዓይነት የተለየ ነገር አይፈጥርም። አርሊንግተን ካውንቲ የአካላስንኩልነት ካርድ እና ታርጋ የተለጠፈላቸው ነዋሪዎች ካውንቲው የመንገድ-ላይ ክፍት ቦታ እንዲተውላቸው የሚጠይቁበት ልዩ መርሀግብር ያቀርባል። የ “የመኖሪያ ስፍራ መንገዶች” የሚለው አርዕስት ስር የእኛን ድረገጽ በመጎብኘት ስለዚህ መርሀግብር የበለጠ ይወቁ።  

ቦርዱ ገንቢዎች ከዞን ትዕዛዝ ከሚጠይቀው በላይ አነስተኛ የሆኑ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች አፓርታማዎች እና ኮንዶሚኔሞችን እንዲገነቡ ይፈቅድላቸዋል። እዚያ የሚኖሩ ሰዎች የ RPP ፈቃዶችን እና ማለፊያዎችን ለምን አያገኙም?

ቦርዱ አዲስ ቤቶችን ለሚገነቡ ገንቢዎች ከዞን ትዕዛዝ ውጪ አነስተኛ የሆነ የመኪና ማቆሚያ እንዲገነቡ የሚፈቅድላቸው በሚከተሉት የፈቃድ መስጫ ሂደት መሰረት ነው፦  

በእዚህ መልኩ የጸደቁ ህንፃዎች ለ RPP የፊርማ ማሰባሰብ ጥያቄ ሊያቀርቡ አይችሉም

የፊርማ ማሰባሰብ ጥያቄ ሂደት

የታቀደው መርሀግብር ላይ የፊርማ ማሰባሰብ ጥያቄ ሂደቱ እንዴት ይቀየራል?

በታቀደው መርሀግብር ውስጥ፣ በብሎኩ ውስጥ የሚገኙት 80% የሚሆኑት አባወራ ቤተሰቦች ገደቦችን ለመደገፍ ፊርማ ማሰባሰብ ጥያቄ መጠየቅ አለባቸው፣ ይሄ ዛሬ ካለው 60% በላይ ከፍ ሊል ይገባል። 

ገደቦችን መጠየቅ ላይ ብቁ ለመሆን፣ ካውንቲው ብዙ ጊዜ ላይ በፊርማ ማሰባሰብ ጥያቄ የቀረበባቸው ብሎኮች ላይ ከ 85% የሚያህሉት የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች እንደሚያዙ ማወቅ አለበት፣ ይሄም አሁን ካለው 75% ከፍ ብሏል። የታቀደው መርሀግብር 25% “ከቦታ-ውጪ” ፈተናን ያስቀራል። 

በተጨማሪም፣ የፊርማ ማሰባሰብ ጥያቄው ለመላው ብሎክ፣ መቋረጫ እስከ መቋረጫ (ወይም ከአንድ መቋረጫ እስከ መንገዱ መጨረሻ ድረስ) የመንገዱ ሁለቱም ጎን ላይ ከሚገኙ አባወራ ቤተሰቦችን ማካተት ያስፈልገዋል። ይሄ ከአሁኑ፣ 100-አድራሻ ብሎክ (ለምሳሌ 1800 S ምሳሌ መንገድ እስከ 1899 S ምሳሌ መንገድ) ውስጥ የሚገኙት ሁሉም አባወራ ቤተሰቦች የፊርማ ማሰባሰብ ጥያቄ ከሚያነሱበት የተለየ ይሆናል።

የታቀደው መርሀግብር የመያዝ ገደብ አሳድጎ “ከቦታ-ውጪ” ፈተና ያስወገደበት ምክንያት ምንድን ነው?

የ RPP መርሀግብር ካውንቲው በብሎኩ ላይ የሚገኙ 75% የሚያህሉት የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች እንደሚያዙ እና 25% የሚያህሉት ክፍት ቦታዎች ደግሞ በአቅራቢያ አድራሻ በሌላቸው (“ከቦታው-ውጪ” በሆኑ) መኪናዎች እንደሚያዙ ገደቦችን ለመስጠት ለረጅም ጊዜ ሲጠይቅ ነበር። 

የታቀደው መርሀግብር 25% “ከቦታ-ውጪ” ፈተና አስወግዷል ምክንያቱም የሞተር መኪናዎች መምሪያ እና የገቢዎች መረጃ ኮሚሽነር ምንጮች ለዚያ ዓላማ “ከቦታ-ውጪ” ብሎ አንድን መኪና ለመፈረጅ ትክክለኛ ገላጭ እንዳልሆኑ ደርሰውበታል።  ለምሳሌ፣ አንድ መኪና ገደቦች እንዲደርግ የፊርማ ማሰባሰብ ጥያቄ የሚጠይቅባቸው መንገዶች ላይ የሚገኝ ነዋሪ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ባለቤቱ መኪናውን በሚገባ ሁኔታ እንዲመዘገብ ላያደርግ ይችላል።   በተጨማሪም፣ በዚያ መንገድ ላይ ካውንቲው ጥናት ሲያከናውን ጊዜ የፊርማ ማሰባሰብ የተጠየቀበት መንገድ ላይ ከተማ ውጪ የሚኖር ሰው አንድ ሰው ቤቶቹን ሲጎበኝ ጊዜ፣ ምንም እንኳን እዛ የመጡት አንድን ነዋሪ ለመጎብኘት ቢመጡም መኪናው “ከቤት ውጪ” ተብሎ ይቆጠራል።  

ከቦታ-ውጪ ፈተናን ማስቀረት፣ አጠቃላዩን የቦታ መያዝ ገደብ 75% እንደሆነ እንዲቀጥል በማድረግ፣ የ RPP ገደቦችን ለማግኘት ቀላል ያደርገዋል እና “ከነዋሪዎች ጋር የመንገድ-ላይ የመኪና ማቆሚያን አጠቃቀም አሟጦ የመጠቀም’ ፍላጎት በማስተር ትራንስፖርት ዕቅድ ላይ ከተጠቀሰው ከአመቺ የሆነ የመንገድ-ላይ መኪና ማቆሚያ ጋር ያለውን ሚዛን ይቀይራል። የታየዘ ቦታ ገደብ ወደ 85% ማሳደግ እና 25% ከቦታ-ውጪ ፈተናን በማስቀረት ያንን ሚዛን የመጠበቂያ መንገድ ይሆናል።

የፊርማ መሰብሰብ ጥያቄ ገደብ ለምን ከፍተኛ መሆን አስፈለገ?

የ RPP መርሀግብር አነጋጋሪ ነው፣ አንዳንድ ነዋሪዎች የመኪና ማቆም ሂደት አመቺ እንዲሆን ማድረግ ወሳኝ እንደሆነ ያስባሉ፣ ሌሎች ደግሞ የሕዝብ ክፍት ቦታን ሰዎች በቀላሉ እንዳይደርሱበት የሚያደርግ ያልተገባ መንገድ እንደሆነ አድርገው ያዩታል። በተጨማሪም፣ አንዴ ገደቦች ከተቀመጡ በኋላ፣ ለረጅም ጊዜ ያህል የመቆየት አዝማሚያ አላቸው። በእነዚህ ምክንያቶች የተነሳ፣ የታቀደው መርሀግብር የ RPP ገደቦች ላይ በፊርማ የማሰበሰብ ጥያቄን በአንድ ብሎክ ላይ የሚኖሩ ከሞላ ጎደል ሁሉም ነዋሪዎች እንዲያቀርቡት ይጠይቃል።

የ RPP ገደቦችን ትግበራ 

ነባሮቹ የ RPP ዞኖች የሚተገበሩበት ሰዓት ይቀየራል?

አይ። ለነባሮች RPP ዞኖች የትግበራ ሰዓታት በነዋሪዎቹ በሚቀርቡ የፊርማ ማሰባሰብ ጥያቄዎች ብቻ ይቀየራል።

ልክ እንደ አዲሱ መርሀግብር አካል የትግበራ መጠኑ ይጨምር ይሆናል?

አይ። ለ RPP ጥሰቶች ፖሊስ የሚከታተልበት እና ትኬት የሚቆርጥበት ብዛት የዚህ ግምግማ አካል ያልሆኑት፣ የፖሊስ ግብዓቶች እና አሰራሮች ላይ ይወሰናል።

የፖሊሲው ለውጦች እንዴት ትግበራውን ቀላል እና የፈቃድ ባልተገባ ሁኔታ መጠቀምን ሊቀንሱ ይችላሉ?

ይሄ የታቀደው መርሀግብር ነዋሪዎች ለእነሱ እና ለእንግዶቻቸው የሚመች መርሀግብር መካከል ያለውን የፍላጎት ሚዛን ለማመጣጠን የሚሞክር እና አመቺነት ያለው መርሀግብር ለመተግበር አዳጋች እንደሆነ የሚረዳ ነው።  

ፈቃድን ያለአግባብ መጠቀም እና በስራ ላይ ማዋል 2018 በካውንቲው የተደረገው አሳታፊ ዝግጅት ላይ በብዛት ውይይት የተደረገባቸው ርእሶች ናቸው።  ሆኖም ግን፣ የ 2019 የአባወራ ቤተሰብ የዳሰሳ ጥናት ላይ፣ በብሎካቸው ላይ RPP ገደቦች ካላቸው አራት ሰዎች ውስጥ አንዱ ነዋሪ ካውንቲው መርሀግብሩ በቀላሉ እንዲተገበር ለማድረግ የፈቃድ ዓይነቶቹን እንዲያቃልል ወይም እንዲቀንስ ይፈልጋሉ። ለመተግበር አመቺ ወይም ደግሞ ቀላል የሆነ መርሀግብር እንደሚፈልጉ ሲጠየቁ ጊዜ፣ በ RPP መርሀግብር ውስጥ ከሚገኙት ነዋሪዎች ግማሾቹ አዋጪነት ይመርጣሉ።  

ምንም እንኳን የፍሌክስፓስ እና የአጭር-ጊዜ የጎብኚ ማለፊያ ለመሸጥ ወይም በዞን ውስጥ ለማይኖር ለሌላ ሰው ለማስተላለፍ ቀላል ቢሆንም፣ የታቀደው መርሀግብር የጎብኚዎች መኪና ማቆሚያ አማራጮችን አመቺ እንዲሆኑ ያደርጋል።  በአንድ አባወራ ቤተሰብ ውስጥ የሚሰጠውን የመጨረሻ የፈቃድ ቁጥር በመቀነስ፣ እያንዳንዱ ፍሌክስፓስ ለነዋሪው የበለጠ ጠቃሚ ይሆናል፣ ይሄ ቤቱን ለማይጎበኙ ሌሎች ሰዎች ፍሌክስፓሱን ከመሸጥ ወይም ከመስጠት ይከላከላል።

የሚሸጡ ሰዎችን ወይም ሊይዙት ለማይገባ ሰዎች ከሚያስተላልፉ ሰዎች ለመከላከል ፍሌክስፓስ መስጠት ለምን አይቆምም?

ፍሌክስፓስ ማስቀረት በተደጋጋሚ ለሚመጡ ጎብኚዎች ወይም መኪና ለማቆም ፍሌክስፓስ ለሚጠቀሙ የቤት ውስጥ ሰራተኞች በሚገባ መልኩ ይሄንን ማለፊያ ለሚጠቀሙ ነዋሪዎች መኪና ማቆም ስራን የበለጠ አዳጋች ያደርጋል።